ውክልና መስጠት ይፈልጋሉ?

ማሳሰቢያ: በአሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ  ባወጣው አዲስ መመሪያ መሰረት እርስዎ ኢትዮጵያ ላለ ሰው ውክልና መስጠት ካለብዎት ውክልናው በኤምባሲ የሰነዱ ትክክለኛነት መረጋገጥ ይኖርበታል። ነገር ግን ከጥር 1፣2010 ዓም ጀምሮ የአሰራር ለውጥ ተደርጓል ።

ከዚህ በፊት ጊዜው ያላለቀ የኢትዮጵያ ፓስፖርት የያዙ ኢትዮጵያውያን እና ያልተቃጠለ የትውልድ ኢትዮጵያውያን ካርድ ለያዙ ግለሰቦች ወደ ኢምባሲው በኖተሪ ፓፕሊክ የተረጋገጠውን ሰነድ በፖስታ ቤት ከተገቢው ክፍያ ጋር በመላክ ማስፈፀም ይችሉ ነበር ፣ ነገር ግን አዲሰ በወጣው መመሪያ መሰረት ዋሽንግተን ዲሲ ያለው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ደንበኞችን በአካል የማያስተናግድ መሆኑን ሲያስታውቅ፣ የሎስ አንጀለሱ የኢትዮጵያ ኢንባሲ ደግሞ ጊዜው ያላለቀ የኢትዮጵያ ፓስፖርት የያዙ ኢትዮጵያውያን እና ያልተቃጠለ የትውልድ ኢትዮጵያውያን ካርድ ለያዙ ግለሰቦች እንዲሁም በአሜሪካው ዲፓርትመንት ኦፍ ስቴት የተረጋገጠ ሰነድ ላያዙ የውጭ አገር ዜጎቸ ባለ ጉዳዮችን በአካል ከቀረቡ እንደሚያስተናግድ በሁለቱም የኢንባሲወች ድረ_ገፅ ላይ ተለጥፏል።

ታዲያ እርስዎ ያለበዎትን የጊዚ ውጥረት እና የገንዘብ ወጪ በመረዳት ይህንን ሂደት እርስዎ ያሉበትን ከተማ ሳይለቁ እኛ ጉዳዮን ከ ሀ – ፐ እናስጨርሳለን። ይህንን አገልግሎት ዜግነታቸውን ለቀየሩ እና ነገር ግን የትውልድ ኢትዮጵያውያን ካርድ ለሌላቸው ባለ ጉዳዮችንም ሁሉ እንደምናሰተነግድ ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው ።

ድርጀታችን ይህንን እገልግሎት ሲሰጥ ከ 20 ዓመት በላይ የስራ ልምድ ሲኖረን ፣ ከነዚም አገለግሎት በተጨማሪ ድርጀታቸን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች ይሰጣል

1 የፓስፖርት እና የቪሻ የማወጣት አገልግሎት
2 የትውልድ ኢትዮጵያዊ ካርድ ማውጣት አገልግሎት
3 የጉዞ አገልግሎት
4 አመታዊ የታክስ ገቢ በኤሌክትሮኒክስ የማስመዝገብ (eFile) አገልገሎት
5 የ DHL አገልግሎት
6 የትርጉም ስራ አገልግሎት አና ሌሎችንም አገልግሎቾች እንሰጣለን።
በበለጠ ለመረዳት በስልክ ቁጥር 619-255-5530 ይደውሉልን ወይም ድረ ገጻችንን WWW.YEBBO COM ወይም WWW.WIKILINA.COM የጎብኙ::

የቦ ኮሚኒኬችን ኔትዎርክ

 

Comments are Closed