ሊሴ ፓሴ

ሊሴ ፓሴ ለማመልከት

  • የአገልግሎት ግዜውን ያበቃ ፓስፖርትዎ ለመለወጥ ወይም ለማሳደስ በቂ ግዜ ከሌለዎትና በተለያየ አስቸኳይ ምክንያት ወደ አገርቤት ለመጓዝ ከፈለጉ ሌሴ ፓሴ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  • ሊሴ ፓሴው ለአንድ ግዜ ወደ ኢትዮጵያ መግቢያ ብቻ የሚያገለግል በመሆኑ ሲመለሱ ከኢትዮጵያ ፓስፖርት ማውጣት እንዳለብዎ አይዘንጉ፡፡
  • ፓስፖርትዎ ተዘጋጅቶ እስከሚደርስዎ ድረስ መቆየት የማይችሉና በተለያየ አጣዳፊ ምክንያቶች በአስቸኳይ ወደ አገርቤት መሄድ ከፈለጉ ወደ አገር ቤት መግቢያ የሚያገለግለውን ሊሴ ፓሴ ብቻ (የሊሴ ፓሴ አገልግሎት የሚለውን ይክፈቱ) ወስደው ከአገር ቤት ፓስፖርት ማመልከት ይገባዎታል።

  • የፓስፖርትና የሊሴ ፓሴ ማመልከቻ በአንድ ላይ ማቅረብ ወይም የፓስፖርትዎ ማመልከቻ ከኤምባሲው ወደ አገር ቤት ከተላከ ከአንድ ወርና ከዚያ በላይ ሳይሆን ሊሴ ፓሴ ማመልከት አይቻልም። ነገር ግን ኢምባሲው ማመልከቻዎን አገር ቤት ከላከ አንድ ወርና ከዚያ በላይ ከሆነና ፓስፖርቱን ሳይረከቡ ጉዞዎ ከደረሰ ሊሴ ፓሴ ወስደው አገር ቤት ሲደርሱ ከኢሚግሬሽን ፓስፖርትዎን መረከብ ይችላሉ።

የፖስታ አላላክ መመሪያ

  • በፖስታ ቤት አማካኝነት ሊሴ ፓሴ የምትጠይቁ ባለጉዳዮች መላኪያም ሆነ መመለሻ ፖስታ መጠቀም የሚኖርባችሁ Tracking Number ባለው FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS MAILመሆን ይገባዋል፡፡
  • የላኩት ፖስታ ወደ ኤምባሲያችን ለመድረሱ ፖስታውን በላኩበት  የTracking Number በመጠቀም ማወቅ ስለሚችሉ እባክዎት ፖስታውን  ኤምባሲ መድረሱን ለማወቅ አይደውሉ፡፡
  • የሊሴ ፓሴዎ ማመልከቻ ኤምባሲው ከተረከበት ከሁለት ውይም ከሶስት የስራ ቀናት በኋላ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ በላኩት የመመለሻ ፓስታ Tracking Number በመጠቀም ያጣሩ!

መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

1

3 የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)

2

አገልግሎቱ ያበቃዉን ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ ኮፒ ማቅረብ

3

ፓስፖርትዎ ከተጠፋ ወይም ከሌሎዎት የትና መቼ እንደወሰዱት የሚገልጽ ማስታወሻ እንዱሁም በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የልደት ማስረጃ በሁለት ኮፒ ማቅረብ

4

በአሜሪካንአገርያሉበትንስታተስየሚያሳይማስረጃ ኮፒ

  • የግሪን ካርድ  ወይም
  • ግሪን ካርድ ከሌለዎት የኢሚግሬሽን ስታተስዎን የሚያሳይ ማስረጃ ወይም
  • የ I-94 ኮፒ ወይም
  • የስራፍቃድ

5

የአገልግሎት ክፍያ $20.00 ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ

  • መኒ ኦርደር /Money Order/ ወይም
  • ካሽየር ቼክ /Cashier Check/ ወይም
  • ሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/

6

መጠየቂያ ቅጽ መሙላት (click here to download FORM)

7

የሊሴ ፓሴው ማመልከቻ በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ

Leave a Reply