ሰነድ ማረጋገጥ

የተለያዩ ሰነዶችን ማረጋገጥ አገልግሎት

እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንስጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈለጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒያቸው አያይዘው ያቅርቡ/ይላኩ፡፡

 • ማንኛውም ለማረጋገጥ የሚመጣው ዶኩመንት ከአሜሪካን መንግስት የመነጨ ከሆነ (ለምሳሌ – ያላገቡ መሆነዎትን የሚያረጋግጥ፣  የልደት የምስክር ወረቀት እና የመሳሰሉትን …) መጀመሪያ ካሉበት አካባቢ ወደሚገኘው ስቴት ኦፊስ በመሄድ ዶኩመንቱን ካረጋገጡ በኋላ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ስቴት ዲፓርትመንት ተረጋግጦ ወደ እኛ መምጣት አለበት፡፡
 • ለማረጋገጥ የሚፈልጉት ዶኩመንት ከኢትዮጵያ የመነጨና በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ ከሆነ በቀጥታ ወደኛ በመላክ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ
 • አገልግሎቱን በፓስታ ቤት በኩል ለምትጠይቁ አመልካቾች እባክዎ መላኪያዎም ሆነ መመለሻ ፖስታዎ ትራኪንግ ቁጥር ባለው የፖስታ አገልግሎት እንዲጠቀሙ እንመክራለን፡፡
የፖስታ አላላክ መመሪያ

 • በፖስታ ቤት አማካኝነት የተለያዩ ሰነዶች ለማረጋገጥ የምትጠይቁ ባለጉዳዮች መላኪያም ሆነ መመለሻ ፖስታ መጠቀም የሚኖርባችሁ Tracking Number ባለው FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS MAILመሆን ይገባዋል፡፡

 • የላኩት ፖስታ ወደ ኤምባሲያችን ለመድረሱ ፖስታውን በላኩበት  የTracking Number በመጠቀም ማወቅ ስለሚችሉ እባክዎት ፖስታውን  ኤምባሲ መድረሱን ለማወቅ አይደውሉ፡፡
 • የተለያዩ ሰነዶች ለማረጋገጥ የላኩት ሰነድ ኤምባሲው ከተረከበት ከሁለት ውይም ከሶስት የስራ ቀናት በኋላ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ በላኩት የመመለሻ ፓስታ Tracking Number በመጠቀም ያጣሩ!

 ሀ በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ ከኢትዮጵያ ለመጡ የተለያዩ ሰነዶችን ለማረጋገጥ

መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

1

መጀመሪያ ለማረጋገጥ የሚፈለገው ዶኩመንት በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤት ተረጋግጦ ማቅረብ

2

የአገልግሎት ክፍያ መጠን

3

 • የታደሰ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ  ኮፒ በማቅረብ 58.50 ዶለር ክፍያ ሲፈፅሙ
 • የሌላ አገር ዜጋ ለሆኑ/በትውልድ ኢትዮጵያዊ  መታወቂያ ካርድ የሌላቸው/ አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት የሌላቸው 94.80 ክፍያ ይፈፅሙ
 • ክፍያው ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ፡­­-

 

 • መኒ ኦርደር /Money Order/ ወይም
 • ካሽየር ቼክ /Cashier Check/ ወይም
 • ሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/

4

የመጠየቂያ ቅጽ መሙላት (click here to download a form)
5

ሰነዱን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ

ለ. ከአሜሪካን መንግስት ለተሰጡ የተለያዩ ዶክመንቶችን ለማረጋገጥ

መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

1

ሰነዱን መጀመሪያ ባሉበት ስቴት ኦፊስ ማረጋገጥ

2

በመቀጠል ዋሽንግትን ዲሲ በሚገኘው ስቴት ዲፓርትመንት አረጋግጦ ማቅርብ

3

የአገልግሎት ክፍያ መጠን

 

 • የታደሰ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ  ኮፒ በማቅረብ 58.50 ዶለር ክፍያ ሲፈፅሙ
 • የሌላ አገር ዜጋ ለሆኑ/በትውልድ ኢትዮጵያዊ  መታወቂያ ካርድ የሌላቸው/ አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት የሌላቸው 94.80 ክፍያ ይፈፅሙ
 • ክፍያው ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ፡­­-

 

 • መኒ ኦርደር /Money Order/ ወይም
 • ካሽየር ቼክ /Cashier Check/ ወይም
 • ሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/
4 የመጠየቂያ ቅጽ መሙላት (click here to download a form)

5

ሰነዱን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ

Leave a Reply