የትውልድ መታወቂያ ካርድ

Your Global passport and Visa center.
Do you need a perfect passport or visa photo that will pass or exceeds government guidelines? Well we have both digital or print photos. We support US Passport, US Visa, US Immigration, US Citizenship, Canadian Passport , Canadian Visa, Canadian Citizenship, Mexican Passport, Mexican Visa, Chinese passport, Chinese Visa,

ሀ. በትውልድ ኢትዮጵያዊ ሆነው ለመጀመሪያ ግዜ መታወቂያ ካርዱን ለሚጠይቁ
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1 የታደሰ የውጭ አገር ፓስፖርት ሁለት ኮፒ
2 የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ በሁለት ኮፒ ማቅረብ
3 ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤት የተረጋገጠ የልደት ማስረጃ በሁለት ኮፒ ማቅረብ
4 ሶስት (3) የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶ ግራፍ(ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)
5 የአገልግሎት ክፍያ 100ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ
መኒ ኦርደር /Money Order/ ወይም | ካሽየር ቼክ /Cashier Check/ ወይም | ሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/
6 መጠየቂያ ቅጽ-1 በሁለት ኮፒ መሙላት (click here to download)

ለ. በትውልድ ኢትየጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኖራቸው ለባለቤታቸው ለሚጠይቁ
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1 የታደሰ የውጭ አገር ፓስፖርት ሁለት ኮፒ
2 የጋብቻ የምስክር ወረቀት ከተሰጠበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤት የተረጋገጠ የጋብቻ ምስክር ወረቀት ሁለት ኮፒ (ጋብቻው ቢያንስ ለሁለት አመት የፀና መሆን ይኖርበታል)
3 ሶስት (3) የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶ ግራፍ(ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)
4. የአገልግሎት ዘመኑ ያላበቃ የአመልካች ወይም ባለቤት የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ሁለት ኮፒ

4 የአገልግሎት ክፍያ 100ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ
መኒ ኦርደር /Money Order/ወይም | ካሽየር ቼክ /Cashier Check/ ወይም | ሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/
5 መጠየቂያ ቅጽ-2 በሁለት ኮፒ መሙላት (click here to download)

ሐ. መታወቂያ ካርዱ የአገልግሎት ዘመኑ በማለቁ ለማሳደስ ለሚጠይቁ
ያለዎት መታወቂያ ካርድ ማንዋል (ቢጫው) ከሆነ ባሉት ሶስት ገጻች ላይ ታድሶ ሊሠጠዎ ወይም በአካል መቅረብ ሳያስፈልግዎ Tracking Number ባለው (FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL) መመለሻ ፓስታ ከነቴምብሩ አያይዘውልን ሲልኩልን ታድሶ በአድራሻዎ ሊላክልዎት ይችላል፡፡ እንዲታደስ ያቀረቡት መታወቂያ ካርድ የሚታደስበት ገጽ ከሌለው ግን በአካል ቀርበው የተዘጋጀልዎትን ተለዋጭ መታወቂያ ካርድ ፈርመው መረከብ ይኖርበታል፡፡
ያለዎት መታወቂያ ካርድ ማሽን ሪደብል (አዲስ አበባ ከሚገኘው ከዋናው መ/ቤት የሚሰጠው) ከሆነ እዚያው ላይ ማሳደስ ስለማይቻል የተዘጋጀለዎትን ተለዋጭ መታወቂያ ካርድ በአካል ቀርበው መረከብ ይኖርቦታል፡፡

መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1 አገልግሎት ዘመኑ ያበቃው የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ዋናውንና ሁለት ኮፒውን ማቅርብ
2 የታደሰ የውጭ አገር ፓስፖርት ሁለት ኮፒ
3.ሶስት (3) የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶ ግራፍ(ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)
4 የአገልግሎት ክፍያ 40ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ መኒ ኦርደር /Money Order/ወይም | ካሽየር ቼክ /Cashier Check/ ወይም | ሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/
5 መጠየቂያ ቅጽ በሁለት ኮፒ መሙላት (click here to download)
መ. በጠፋ ወይም በተበላሸ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ምትክ ለሚጠይቁ
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1 የታደሰ የውጭ አገር ፓስፖርት በሁለት ኮፒ
2. የቀድሞ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ሁለት ኮፒ (የመታወቂያ ኮፒ ከሌለዎት መቼ እና ከየት እንደወሰዱት የሚገልፅ ማስታወሻ አያይዘው ይላኩ)
3 ሶስት (3) የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶ ግራፍ(ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)
4የአገልግሎት ክፍያ 60ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ
መኒ ኦርደር /Money Order/ወይም | ካሽየር ቼክ /Cashier Check/ ወይም ሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/
5 መጠየቂያ ቅጽ በሁለት ኮፒ መሙላት (click here to download)

ሠ. ሲጠቀሙበት የነበረ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለመመለስ ለሚጠይቁ

መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1 የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያውን ማቅረብ
2 መታወቂያው በፍላጎትዎ የሚመልሱ ለመሆኑ ማስታሻ ጽፈውና ፈርመው ማቅረብ
3 መጠየቂያ ቅጽ-4 መሙላት

Source Ethiopian Embassy. Please refer the embassy’s web site for up to date information

Leave a Reply