ፓስፖርት
-
እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንስጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈለጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒያቸው አያይዘው ያቅርቡ/ይላኩ፡በኢትዮጵያ ኢሚግሬሽን ሲሰጥ የነበረው አዲሱ ማሽን ሪደብል ፓስፖርት እ.ኤ.አ ኤፕሪል 2010 ጀምሮ በኢምባሲያችን በኩል አገር ቤት ተልኮ መሰጠት ስለተጀመረ እባክዎ ከጉዞ ቀን ወይም ከታደሰ ፓስፖርት ጋር በተያያዘ አገልግሎት ከመጠየቅዎ ቢያንስ 45 ቀናት አስቀድመው ማመልከት ይጠበቅበታል፡፡
-
አዲሱ ማሽን ሪደብል ፓስፖርት ለማግኘት የጣት አሻራ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀደሞ አዲሱን ፓስፖርት ሲወስዱ የጣት አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ መስጠት አያስፈልግዎትም፡፡ እድሜአቸው ከ14 አመት በታች የሆኑ ህጻናት አሻራ መስጠት አይጠበቅባቸውም፤ ሆኖም ከዚህ ቀድሞ ከ14 ዓመት በታች በመሆናቸው ምክንያት ያለ አሻራ አዱሱ ፓስፖርት ተዘጋጅቶላቸው ከነበረና አሁን ከ14ዓመትና በላይ ከሆኑ የጣት አሻራ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
-
ኢምባሲው ፓስፖርትዎን ለማዘጋጀት ተጨማሪ ማስረጃዎች እንዲያቀርቡ ሲጠይቅ እባክዎ በተነገረዎት በሳምንት ግዜ ውስጥ ማስረጃውን ይላኩልን፡፡ ሆኖም ማስረጃውን እንዲልኩ ለ3ኛ ግዜ ተገልጾልዎት ከሆነና በወቅቱ ካላቀረቡ ፈይልዎ ተመላሽ ተደርጎ እንደ አዲስ ማመልከት ይጠበቅበዎታል፡፡
-
ፓስፖርትዎ ተዘጋጅቶ እስከሚደርስዎ ድረስ መቆየት የማይችሉና በተለያየ አጣዳፊ ምክንያቶች በአስቸኳይ ወደ አገርቤት መሄድ ከፈለጉ ወደ አገር ቤት መግቢያ የሚያገለግለውን ሊሴ ፓሴ ብቻ (የሊሴ ፓሴ አገልግሎት የሚለውን ይክፈቱ) ወስደው ከአገር ቤት ፓስፖርት ማመልከት ይገባዎታል።
-
የፓስፖርትና የሊሴ ፓሴ ማመልከቻ በአንድ ላይ ማቅረብ ወይም የፓስፖርትዎ ማመልከቻ ከኤምባሲው ወደ አገር ቤት ከተላከ ከአንድ ወርና ከዚያ በላይ ሳይሆን ሊሴ ፓሴ ማመልከት አይቻልም። ነገር ግን ኢምባሲው ማመልከቻዎን አገር ቤት ከላከ አንድ ወርና ከዚያ በላይ ከሆነና ፓስፖርቱን ሳይረከቡ ጉዞዎ ከደረሰ ሊሴ ፓሴ ወስደው አገር ቤት ሲደርሱ ከኢሚግሬሽን ፓስፖርትዎን መረከብ ይችላሉ።
-
አገልግሎቱ ያለቀ ፓስፖርት ለመቀየር/ለማደስ
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች 1
4 የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)
2
ለመቀየር ወይም ለማደስ የተፈለገው ዋናው ፓስፖርት ማቅረብ
3
ለመቀየር ወይም ለማደስ የተፈለገው ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ በሁለት ኮፒ ማቅረብ
4
በአሜሪካን አገር ያሉበትን ስታተስ የሚያሳይ ማስረጃ በሁለት ኮፒ
- የግሪን ካርድ ወይም
- ግሪን ካርድ ከሌለዎት የኢሚግሬሽን ስታተስዎን የሚያሳይ ማስረጃ ወይም
- የ I-94 ኮፒ ወይም
- የስራፍቃድ
5
የአገልግሎት ክፍያ $50.00 ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ
- መኒ ኦርደር /Money Order/ ወይም
- ካሽየር ቼክ /Cashier Check/ ወይም
- ሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/
6
የጣት አሻራ ማቅርብ ለሚጠበቅባችሁ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ/መላክ (click here to download Fingerprint Capture FORM)
7
መጠየቂያ ቅጽ በሁለት ኮፒ መሙላት (click here to download FORM)
8
አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ
በጠፋ ፓስፖርት ምትክ አዲስ ፓስፖርት ለመቀየር
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች 1
4 የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)
2
ኢትዮጵያዊነትን የሚያስረዱ ሰነዶች በሁለት ኮፒ ማቅረብ
- የቀድሞ ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ ማቅረብ ወይም
- በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤት የተረጋገጠ የልደት ማስረጃ ወይም
- የቀበሌመታወቂያ
3
በአሜሪካን አገር ያሉበትን ስታተስ የሚያሳይ ማስረጃ በሁለት ኮፒ
- የግሪን ካርድ ወይም
- ግሪን ካርድ ከሌለዎት የኢሚግሬሽን ስታተስዎን የሚያሳይ ማስረጃ ወይም
- የ I-94 ኮፒ ወይም
- የስራ ፍቃድ
4
የአገልግሎት ክፍያ $60.00 ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ
- መኒ ኦርደር /Money Order/ወይም
- ካሽየር ቼክ /Cashier Check/ ወይም
- ሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/
5
የጣት አሻራ ማቅረብ ለሚጠበቅባችሁ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ/መላክ (click here to download Fingerprint Capture FORM)
6
መጠየቂያ ቅጽ በሁለት ኮፒ መሙላት(click here to download FORM)
7
አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ
በወላጆቻቸው ፓስፖርት ተለጥፈው ሲጓዙ ለነበሩ ህጻናት ወይም ከዚህ ቀደሞ በማንኛውም ጊዜና ቦታ ፓስፖርት ያልወሰዱና ለመጀመሪያ ጊዜ ፓስፖርት ለሚጠይቁ
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች 1
4 የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት) 2
ኢትዮጵያዊነትን የሚያስረዱ ሰነዶች በሁለት ኮፒማቅረብ
- ከወላጆቻቸው ጋር የተጓዙበትን ፓስፖርት ኮፒ ወይም
- በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤት የተረጋገጠ የልደት ማስረጃ ወይም
- የቀበሌ መታወቂያ
3
በአሜሪካን አገር ያሉበትን ስታተስ የሚያሳይ ማስረጃ በሁለት ኮፒ
- የግሪን ካርድ ወይም
- ግሪን ካርድ ከሌለዎት የኢሚግሬሽን ስታተስዎን የሚያሳይ ማስረጃ ወይም
- የ I-94 ኮፒ ወይም
- የስራፍቃድ
4
የአገልግሎት ክፍያ $60.00 ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ
- መኒ ኦርደር /Money Order/ወይም
- ካሽየር ቼክ /Cashier Check/ ወይም
- ሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/
5
የጣት አሻራ ማቅረብ ለሚጠበቅባችሁ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ/መላክ (click here to download Fingerprint Capture FORM)
6
መጠየቃ ቅጽ በሁለት ኮፒ መሙላት(click here to download FORM)
7
አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ