ተለያዩ ሰነዶችን ማረጋገጥ አገልግሎት
እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንስጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈለጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒያቸው አያይዘው ያቅርቡ/ይላኩ፡፡ማንኛውም ለማረጋገጥ የሚመጣው ዶኩመንት ከአሜሪካን መንግስት የመነጨ ከሆነ (ለምሳሌ – ያላገቡ መሆነዎትን የሚያረጋግጥ፣  የልደት የምስክር ወረቀት እና የመሳሰሉትን …) መጀመሪያ ካሉበት አካባቢ ወደሚገኘው ስቴት ኦፊስ በመሄድ ዶኩመንቱን ካረጋገጡ በኋላ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ስቴት ዲፓርትመንት ተረጋግጦ ወደ እኛ መምጣት አለበት፡፡ለማረጋገጥ የሚፈልጉት ዶኩመንት ከኢትዮጵያ የመነጨና በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ ከሆነ በቀጥታ ወደኛ በመላክ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉአገልግሎቱን በፓስታ ቤት በኩል ለምትጠይቁ አመልካቾች እባክዎ መላኪያዎም ሆነ መመለሻ ፖስታዎ ትራኪንግ ቁጥር ባለው የፖስታ አገልግሎት እንዲጠቀሙ እንመክራለን፡፡
የፖስታ አላላክ መመሪያበፖስታ ቤት አማካኝነት የተለያዩ ሰነዶች ለማረጋገጥ የምትጠይቁ ባለጉዳዮች መላኪያም ሆነ መመለሻ ፖስታ መጠቀም የሚኖርባችሁ Tracking Number ባለው FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS MAILመሆን ይገባዋል፡፡የላኩት ፖስታ ወደ ኤምባሲያችን ለመድረሱ ፖስታውን በላኩበት  የTracking Number በመጠቀም ማወቅ ስለሚችሉ እባክዎት ፖስታውን  ኤምባሲ መድረሱን ለማወቅ አይደውሉ፡፡የተለያዩ ሰነዶች ለማረጋገጥ የላኩት ሰነድ ኤምባሲው ከተረከበት ከሁለት ውይም ከሶስት የስራ ቀናት በኋላ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ በላኩት የመመለሻ ፓስታ Tracking Number በመጠቀም ያጣሩ!
የተለያዩ ሰነዶች ለማረጋገጥሀ. በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ ከኢትዮጵያ ለመጡ የተለያዩ ሰነዶችን ለማረጋገጥለ. ከአሜሪካን መንግስት ለተሰጡ የተለያዩ ደኮመንቶችን ለማረጋገጥ
 ሀ በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ ከኢትዮጵያ ለመጡ የተለያዩ ሰነዶችን ለማረጋገጥ
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች1መጀመሪያ ለማረጋገጥ የሚፈለገው ዶኩመንት በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤት ተረጋግጦ ማቅረብ2የአገልግሎት ክፍያ መጠን3የታደሰ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ  ኮፒ በማቅረብ 58.50 ዶለር ክፍያ ሲፈፅሙየሌላ አገር ዜጋ ለሆኑ/በትውልድ ኢትዮጵያዊ  መታወቂያ ካርድ የሌላቸው/ አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት የሌላቸው 94.80 ክፍያ ይፈፅሙክፍያው ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ፡­­- መኒ ኦርደር /Money Order/ ወይምካሽየር ቼክ /Cashier Check/ ወይምሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/4የመጠየቂያ ቅጽ መሙላት (5ሰነዱን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክT
ለ. ከአሜሪካን መንግስት ለተሰጡ የተለያዩ ዶክመንቶችን ለማረጋገጥ
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች1ሰነዱን መጀመሪያ ባሉበት ስቴት ኦፊስ ማረጋገጥ2በመቀጠል ዋሽንግትን ዲሲ በሚገኘው ስቴት ዲፓርትመንት አረጋግጦ ማቅርብ3የአገልግሎት ክፍያ መጠን የታደሰ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ  ኮፒ በማቅረብ 58.50 ዶለር ክፍያ ሲፈፅሙየሌላ አገር ዜጋ ለሆኑ/በትውልድ ኢትዮጵያዊ  መታወቂያ ካርድ የሌላቸው/ አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት የሌላቸው 94.80 ክፍያ ይፈፅሙክፍያው ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ፡­­- መኒ ኦርደር /Money Order/ ወይምካሽየር ቼክ /Cashier Check/ ወይምሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/4የመጠየቂያ ቅጽ መሙላት
ሰነዱን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ