Skip to content
ፓስፖርት
- እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንስጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈለጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒያቸው አያይዘው ያቅርቡ/ይላኩ፡በኢትዮጵያ ኢሚግሬሽን ሲሰጥ የነበረው አዲሱ ማሽን ሪደብል ፓስፖርት እ.ኤ.አ ኤፕሪል 2010 ጀምሮ በኢምባሲያችን በኩል አገር ቤት ተልኮ መሰጠት ስለተጀመረ እባክዎ ከጉዞ ቀን ወይም ከታደሰ ፓስፖርት ጋር በተያያዘ አገልግሎት ከመጠየቅዎ ቢያንስ 45 ቀናት አስቀድመው ማመልከት ይጠበቅበታል፡፡
- አዲሱ ማሽን ሪደብል ፓስፖርት ለማግኘት የጣት አሻራ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀደሞ አዲሱን ፓስፖርት ሲወስዱ የጣት አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ መስጠት አያስፈልግዎትም፡፡ እድሜአቸው ከ14 አመት በታች የሆኑ ህጻናት አሻራ መስጠት አይጠበቅባቸውም፤ ሆኖም ከዚህ ቀድሞ ከ14 ዓመት በታች በመሆናቸው ምክንያት ያለ አሻራ አዱሱ ፓስፖርት ተዘጋጅቶላቸው ከነበረና አሁን ከ14ዓመትና በላይ ከሆኑ የጣት አሻራ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ኢምባሲው ፓስፖርትዎን ለማዘጋጀት ተጨማሪ ማስረጃዎች እንዲያቀርቡ ሲጠይቅ እባክዎ በተነገረዎት በሳምንት ግዜ ውስጥ ማስረጃውን ይላኩልን፡፡ ሆኖም ማስረጃውን እንዲልኩ ለ3ኛ ግዜ ተገልጾልዎት ከሆነና በወቅቱ ካላቀረቡ ፈይልዎ ተመላሽ ተደርጎ እንደ አዲስ ማመልከት ይጠበቅበዎታል፡፡
- ፓስፖርትዎ ተዘጋጅቶ እስከሚደርስዎ ድረስ መቆየት የማይችሉና በተለያየ አጣዳፊ ምክንያቶች በአስቸኳይ ወደ አገርቤት መሄድ ከፈለጉ ወደ አገር ቤት መግቢያ የሚያገለግለውን ሊሴ ፓሴ ብቻ (የሊሴ ፓሴ አገልግሎት የሚለውን ይክፈቱ) ወስደው ከአገር ቤት ፓስፖርት ማመልከት ይገባዎታል።
- የፓስፖርትና የሊሴ ፓሴ ማመልከቻ በአንድ ላይ ማቅረብ ወይም የፓስፖርትዎ ማመልከቻ ከኤምባሲው ወደ አገር ቤት ከተላከ ከአንድ ወርና ከዚያ በላይ ሳይሆን ሊሴ ፓሴ ማመልከት አይቻልም። ነገር ግን ኢምባሲው ማመልከቻዎን አገር ቤት ከላከ አንድ ወርና ከዚያ በላይ ከሆነና ፓስፖርቱን ሳይረከቡ ጉዞዎ ከደረሰ ሊሴ ፓሴ ወስደው አገር ቤት ሲደርሱ ከኢሚግሬሽን ፓስፖርትዎን መረከብ ይችላሉ።
- አገልግሎቱ ያለቀ ፓስፖርት ለመቀየር/ለማደስመሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች14 የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)2ለመቀየር ወይም ለማደስ የተፈለገው ዋናው ፓስፖርት ማቅረብ3ለመቀየር ወይም ለማደስ የተፈለገው ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ በሁለት ኮፒ ማቅረብ4በአሜሪካን አገር ያሉበትን ስታተስ የሚያሳይ ማስረጃ በሁለት ኮፒ
- የግሪን ካርድ ወይምግሪን ካርድ ከሌለዎት የኢሚግሬሽን ስታተስዎን የሚያሳይ ማስረጃ ወይምየ I-94 ኮፒ ወይምየስራፍቃድ
5የአገልግሎት ክፍያ $50.00 ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ- መኒ ኦርደር /Money Order/ ወይምካሽየር ቼክ /Cashier Check/ ወይምሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/
6የጣት አሻራ ማቅርብ ለሚጠበቅባችሁ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ/መላክ (click here to download Fingerprint Capture FORM)7መጠየቂያ ቅጽ በሁለት ኮፒ መሙላት (click here to download FORM)8አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክTOPበጠፋ ፓስፖርት ምትክ አዲስ ፓስፖርት ለመቀየርመሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች14 የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)2ኢትዮጵያዊነትን የሚያስረዱ ሰነዶች በሁለት ኮፒ ማቅረብ- የቀድሞ ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ ማቅረብ ወይምበኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤት የተረጋገጠ የልደት ማስረጃ ወይምየቀበሌመታወቂያ
3በአሜሪካን አገር ያሉበትን ስታተስ የሚያሳይ ማስረጃ በሁለት ኮፒ- የግሪን ካርድ ወይምግሪን ካርድ ከሌለዎት የኢሚግሬሽን ስታተስዎን የሚያሳይ ማስረጃ ወይምየ I-94 ኮፒ ወይምየስራ ፍቃድ
4የአገልግሎት ክፍያ $60.00 ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ- መኒ ኦርደር /Money Order/ወይምካሽየር ቼክ /Cashier Check/ ወይምሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/
5የጣት አሻራ ማቅረብ ለሚጠበቅባችሁ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ/መላክ (click here to download Fingerprint Capture FORM)6መጠየቂያ ቅጽ በሁለት ኮፒ መሙላት(click here to download FORM)7አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክTOPበወላጆቻቸው ፓስፖርት ተለጥፈው ሲጓዙ ለነበሩ ህጻናት ወይም ከዚህ ቀደሞ በማንኛውም ጊዜና ቦታ ፓስፖርት ያልወሰዱና ለመጀመሪያ ጊዜ ፓስፖርት ለሚጠይቁመሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች14 የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)2ኢትዮጵያዊነትን የሚያስረዱ ሰነዶች በሁለት ኮፒማቅረብ- ከወላጆቻቸው ጋር የተጓዙበትን ፓስፖርት ኮፒ ወይምበኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤት የተረጋገጠ የልደት ማስረጃ ወይምየቀበሌ መታወቂያ
3በአሜሪካን አገር ያሉበትን ስታተስ የሚያሳይ ማስረጃ በሁለት ኮፒ- የግሪን ካርድ ወይምግሪን ካርድ ከሌለዎት የኢሚግሬሽን ስታተስዎን የሚያሳይ ማስረጃ ወይምየ I-94 ኮፒ ወይምየስራፍቃድ
4የአገልግሎት ክፍያ $60.00 ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ- መኒ ኦርደር /Money Order/ወይምካሽየር ቼክ /Cashier Check/ ወይምሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/
5የጣት አሻራ ማቅረብ ለሚጠበቅባችሁ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ/መላክ (click here to download Fingerprint Capture FORM)6መጠየቃ ቅጽ በሁለት ኮፒ መሙላት(click here to download FORM)7አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ
Share this: