የውክልና አገልግሎት
እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንስጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈለጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒያቸው አያይዘው ያቅርቡ/ይላኩ፡፡
ዜግነትዎ ኢትያጵያዊ ወይም ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካልዎትኤምባሲው ዘንድ በአካል የሚቀርቡ ከሆነ የውክልና ሰነዱን ኦፊሰሩ ባለበት ፈርመው ማስፈፀም ይኖርበታልውክልናው በመልዕክት / mail / የሚልኩ ከሆነ ሰነዱን ኖተራይዝ አድርገው አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ
የሌላ አገር ዜጋ ለሆኑ/በትውልድ ኢትዮጵያዊ  መታወቂያ ካርድ የሌላቸው/ አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት የሌላቸው
ውክልናውን በአማርኛና በእንግለሊዘኛ ተጽፎ ኖተራይዝ በማድረግ በመጀመሪያ ባሉበት ስቴት ኦፊስ ቀጥሎ ዋሽንግተን ዲሲ ወደሚገኘው ስቴት ዲፓርትመንት በመላክ አረጋግጦ መቅረብ/መላክአገልግሎቱን በፓስታ ቤት በኩል ለምትጠይቁ አመልካቾች እባክዎ መላኪያዎም ሆነ መመለሻ ፖስታዎ ትራኪንግ ቁጥር ባለው የፖስታ አገልግሎት እንዲጠቀሙ እንመክራለን፡፡
የፖስታ አላላክ መመሪያበፖስታ ቤት አማካኝነት ውክልና የምትጠይቁ ባለጉዳዮች መላኪያም ሆነ መመለሻ ፖስታ መጠቀም የሚኖርባችሁ Tracking Number ባለው FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS MAILመሆን ይገባዋል፡፡የላኩት ፖስታ ወደ ኤምባሲያችን ለመድረሱ ፖስታውን በላኩበት  የTracking Number በመጠቀም ማወቅ ስለሚችሉ እባክዎት ፖስታውን  ኤምባሲ መድረሱን ለማወቅ አይደውሉ፡፡የውክልናዎ ማመልከቻ ኤምባሲው ከተረከበት ከሁለት ውይም ከሶስት የስራ ቀናት በኋላ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ በላኩት የመመለሻ ፓስታ Tracking Number በመጠቀም ያጣሩ!
የውክልና አገልግሎቶችሀ. አትዮጵያዊ ዜግነት ላላቸውለ. ትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለያዙሐ. የሌላ አገር ዜጋ ለሆኑ/በትውልድ ኢትዮጵያዊ  መታወቂያ ካርድ የሌላቸው/ አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት የሌላቸው
 ሀ የአትዮጵያዊ ዜግነት ላላቸው
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች1ውክልናውን አዘጋጅቶ ማቅረብ/መላክ2የታደሰ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ኮፒ3በአሜሪካን አገር ያሉበትን ስታተስ የሚያሳይ ማስረጃ  ኮፒ የግሪን ካርድ  ወይምግሪን ካርድ ከሌለዎት የኢሚግሬሽን ስታተስዎን የሚያሳይ ማስረጃ ወይምየ I-94 ኮፒ ወይምየስራ ፍቃድ5የአገልግሎት ክፍያ 61.20 ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈመኒ ኦርደር /Money Order/ ወይምካሽየር ቼክ /Cashier Check/ ወይምሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/6የመጠየቂያ ቅጽ መሙላት (Click here to download a Form)7ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ
ለ. ትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለያዙ
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች1ውክልናውን አዘጋጅቶ ማቅረብ/መላክ2የታደሰ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኮፒ3የአገልግሎት ክፍያ 61.20 ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈመኒ ኦርደር /Money Order/ ወይምካሽየር ቼክ /Cashier Check/ ወይምሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/4የመጠየቂያ ቅጽ መሙላት(Click here to download a Form)5ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክTOPሐ. የሌላ አገር ዜጋ ለሆኑ/በትውልድ ኢትዮጵያዊ  መታወቂያ ካርድ የሌላቸው/ አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት የሌላቸውመሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች1በአማርኛና በእንግሊዘና ጽፈው ያዘጋጅቱን ውክልና በመጀመሪያ ባሉበት ስቴት ኦፊሰር ቀጥሎ  ዋሽንግትን ዲሲ በሚገኘው ስቴት ዲፓርትመንት በመላክ አረጋግጦ ማምጣት2የአገልግሎት ክፍያ 94.80 ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ መኒ ኦርደር /Money Order/ ወይምካሽየር ቼክ /Cashier Check/ ወይምሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/3የመጠየቂያ ቅጽ መሙላት(Click here to download a Form)4ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *