ለአሜሪካና ካናዳ መንገደኞች ጠቃሚ ማስታወሻዎች

Page 1 of 3

1. በሚጓዙበት ወቅት የፓስፖርትዎ የአገልግሎት ጊዜ ቢያንስ ለስድስት ወራት የሚሰራ መሆኑን ያረጋግጡ።
ለአሜሪካና ካናዳ መንገደኞች ጠቃሚ ማስታወሻዎች
2. አስፈላጊውን የመድረሻና ትራንዚት አገር ቪዛ ማግኘትዎን እና ሌሎች ለጉዞዎ የሚያስፈልጉ ሰነዶች
እንዳለዎትና መያዝዎን ያረጋግጡ።
3. የበረራዎን መነሻና መድረሻ ቀንና ሰዓት እንዲሁም አየር ማረፊያ የሚገኙበትን ሰዓት በትክክል ይወቁ ።
እባክዎ በሰዓቱ ይገኙ።
4. ልዩ የምግብ ምርጫ ካለዎት (የፆም፣ የሙስሊም፣ ቬጂቴሪያን – ሥጋ የማይመገቡ ፣ በሃኪም የታዘዘ፣ የህፃናት
ምግብ ወዘተ…) ለበረራ በሚመዘገቡበት ወይም ትኬት በሚቆርጡበት ጊዜ ለምዝገባ ወይም ለትኬት
ሠራተኞቻችን ያስታውቁ።
5. በነፃ ለማጓጓዝ የሚፈቀድልዎት የሻንጣ ብዛትና የክብደት መጠን እንደሚከተለው ነው።
አንደኛ ማዕረግ                                               ሁለተኛ ማዕረግ
(ክላውድ ናይን )                                            (ኢኮኖሚ ክላስ)
ብዛት                                                                             2                                                               2
የአንዱ ሻንጣ ክብደት                              32 ኪሎ ግራም    (70 ፓውንድ)                              23 ኪሎ ግራም  (50 ፓውንድ)

የሻንጣው ጠቅላላ ዙሪያ                                158 ሳ.ሜትር                                                      158 ሳ.ሜትር
(ር + ወ +ቁ)                                             (62 ኢንች)                                                          (62 ኢንች)

ከላይ ከተጠቀሰው ሻንጣ በላይ ከያዙ የትርፍ ሻንጣ ታሪፍ (ተመን) የሚያስከፍል ሲሆን ትርፍ ሻንጣዎም ሆነ
በነፃ ለማጓጓዝ የሚፈቀድልዎ ሻንጣ ክብደቱ ከ32 ኪሎ ግራም (70 ፓውንድ) ያለፈ ከሆነ የማንቀበል መሆኑን
በትህትና እንገልፃለን። በተጨማሪም በካርቶን ፣ በፕላስቲክ ከረጢት ወይም ለማጓጓዝ ጥንካሬ በሌላቸው
መያዣዎች ወይም ቦርሳዎች የሚመጡ ንብረቶችን የማንቀበል መሆኑን በትህትና እንገልጻለን።
6. ከዚህ በታች የሠፈረው የትርፍ ሻንጣ ታሪፍ (ተመን) እንደ በረራው መስመር እና እንደ ሻንጣው ክብደት
ተፈፃሚ ስለሚሆን ሊያስተውሉት ይገባል።
ሀ. ከአዲስ አበባ ወደ ዋሸንግተን ዲሲ ወይም ከዋሸንግተን ዲሲ ወደ አዲስ አበባ የበረራ መስመር ላይ
ክብደቱ እስከ 23 ኪሎ ግራም (50 ፓውንድ) ለሚሆን ትርፍ ሻንጣ 150 የአሜሪካ ዶላር ሲያስከፍል፤
ክብደቱ ከ24 እስከ 32 ኪሎ ግራም (51-70 ፓውንድ) ለሚሆን ትርፍ ሻንጣ 210 የአሜሪካ ዶላር
ያስከፍላል።
ለ. ጉዞውን ከዋሽንግተን ዲሲ በአዲስ አበባ በኩል ወደ ሌሎች ከተሞች ለሚቀጥል መንገደኛ ክብደቱ እስከ
23 ኪሎ ግራም (50ፓውንድ) ለሚሆን ለያዘው ትርፍ ሻንጣ እንደ መድረሻ ጣቢያው ልዩነት ከ150 እስከ
200 የአሜሪካ ዶላር ሲያስከፍል፤ ክብደቱ ከ24 እስከ 32 ኪሎ ግራም (ከ51 -70 ፓውንድ) ለሚሆን
ትርፍ ሻንጣ ደግሞ እንደ መድረሻ ጣቢያው ልዩነት ከ210 እስከ 260 የአሜሪካ ዶላር ያስከፍላል።
ሐ. ጉዞውን ከአዲስ አበባ ተነስቶ በዋሽንግተን ዲሲ በኩል ወደ ሌሎች የአሜሪካ ከተሞች ለሚቀጥል መንገደኛ
ለሚያጓጉዘው ክብደቱ እስከ 23 ኪሎ ግራም (50 ፓውንድ) ለሚደርስ ትርፍ ሻንጣ 200.00 የአሜሪካ
ዶላር ያስከፍላል።
Page 2 of 3
መ. ጉዞውን ከዋሽንግተን ዲሲ ውጭ ከሆኑ ከተሞች ለሚጀምር መንገደኛ እስከ ከዋሽንግተን ዲሲ ድረስ
ያለው የትርፍ ሻንጣ ታሪፍ (ተመን) መንገደኛው በሚጓጓዝበት አየር መንገድ እና በመነሻ ከተማው
ይወሰናል።
ሠ. በሁለተኛ ማዕረግ (በኢኮኖሚ ክላስ) ለሚጓዙ መንገደኞች የተፈቀደው የሻንጣ ብዛት 2 እንዳለ ሆኖ
የተፈቀደውን የክብደት መጠን ማለትም 23 ኪሎ ግራም (50 ፓውንድ) ካለፈ፤ ከ24 እስከ 32 ኪ.ግራም
ለሚሆን ሻንጣ ተጨማሪ 60 የአሜሪካ ዶላር ያስከፍላል።
7. በእጅዎ አውሮፕላን ውስጥ ይዘው ለመግባት የሚፈቀድልዎ የእጅ ሻንጣ ብዛትና የክብደት መጠን

አንደኛ ማዕረግ                                               ሁለተኛ ማዕረግ
(ክላውድ ናይን )                                            (ኢኮኖሚ ክላስ)
ብዛት                                                                             2                                                               2
የአንዱ ሻንጣ ክብደት                              8 ኪሎ ግራም    (17 ፓውንድ)                              7 ኪሎ ግራም  (15 ፓውንድ)

የሻንጣው ጠቅላላ ዙሪያ                               115 ሳ.ሜትር                                                      115 ሳ.ሜትር
(ር + ወ +ቁ)                                             (45 ኢንች)                                                          (45 ኢንች)

እንደሚከተለው ነው።

ሀ. ምግብ ነክ ነገሮች በእጅ ሻንጣዎ ውስጥ መያዝ አይፈቀድም።
ለ. ከላይ በቁጥር 7 ከተፈቀደው መጠንና ክብደት የሚበልጡ ሻንጣዎችን አውሮፕላን ውስጥ ይዞ መግባት
ስለማይቻል ሻንጣው ከእጅ ሻንጣ ምድብ ወጥቶ በነፃ ለማጓጓዝ ከሚፈቀደው ትልቅ ሻንጣ ጋር
እንዲጫን ይደረጋል። ይህ ደግሞ እንደትርፍ ሻንጣ ስለሚቆጠር በቁጥር 6 በተገለጸው የትርፍ ሻንጣ
ክፍያ መሠረት ይስተናገዳል። (ይህ ካልሆነ ሻንጣውን እንዲመልሱ ይገደዳሉ)
B. ስምዎንና አድራሻዎን ከሻንጣዎ ውስጥና ውጭ በትክክል መፃፍዎን አይዘንጉ። ይህም ምናልባት አየር
መንገዱ በሻንጣው ላይ የሚለጥፈው መለያ ቁጥር ወይም ታግ ቢጠፋ ሻንጣዎን በቀላሉ ለመለየት
ይረዳል።
መ. እንደ ጥሬ ገንዘብ፣ ጌጣጌጥ፣ ካሜራና ውድ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በእጅዎ በሚይዙት ሻንጣ
ውስጥ ያስቀምጡ። የያዙት የእጅ ሻንጣ መጠን በቁጥር 7 ከተፈቀደው መጠንና ክብደት በላይ ሆኖ
ከተገኘና በነፃ ለማጓጓዝ ከሚፈቀደው ሻንጣ ጋር እንዲጫን ከታዘዘ ውድ ንብረቶችዎን አውጥተው
መያዝዎን ልብ ይበሉ። አየር መንገዱ ውድ ለሆኑ ዕቃዎች መበላሸት፣ መሰበር ወይንም መጥፋት
ተጠያቂነትን እንደማይወስድ በትህትና እንገልፃለን።
ሠ. በእጅዎ በሚይዙት ሻንጣ(ዎች) ውስጥ መጠኑ ከ85 ሚሊ ሊትር በላይ የሆነ ማንኛውንም ፈሳሽ ነገር
ይዞ መጓዝ አይፈቀድም። ሆኖም መድሃኒት፣ የህፃናት ምግብ፣ ወተት ከ3 አውንስ (85 ሚሊ ሊትር)
በላይ ይዘው ከሆነ ለደህንነት ክፍል ባለሞያዎች (ሴኩሪቲ) አሳውቆ በእጅ ሻንጣ ይዞ መጓዝ ይቻላል።
ረ. በእጅዎ በሚይዙት ሻንጣ ውስጥ አርተፊሻል ሽጉጥ፣ ምላጭ፣ ስለታማ የምግብ መገልገያዎች፣ ቢላዋ ፣
መቀስ፣ የሹራብ መሥሪያ ሽቦ እና የመሳሰሉትን ይዞ ወደ አውሮፕላን ውስጥ መግባት አጥብቆ
የተከለከለ ነው።
8. ለእርስዎና ለበረራው ደህንነት ሲባል ከማንኛውም ሰው ምንነቱን የማያውቁትን ዕቃ ወይም ጥቅል ይዞ መገኘት
Page 3 of 3
በቀጥታ ራስዎን በኃላፊነት ስለሚያስጠይቅዎ እንዳይቀበሉ በጥብቅ እናሳስባለን። ለጥንቃቄ እንዲረዳዎ ለጉዞ
ያሰናዱትን ሻንጣ ለአየር መንገዱ እስኪያስረክቡ ድረስ ሻንጣዎ በቁጥጥርዎ ሥር እንዲሆን እና ባዕድ ነገር
በማያውቁት መንገድ እንዳይገባ ይከላከሉ። በሻንጣዎ ውስጥ የያዙትንም ንብረት ጠንቅቀው ይወቁ።
9. በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የመንገደኞች መቀበያ ካውንተሮቻችን ከበረራው መነሻ ሶስት ሰዓት
አስቀድመው ሥራ ይጀምራሉ። የሁለተኛ ማዕረግ (የኢኮኖሚ ክላስ) ካውንተሮች በረራው አንድ ሰዓት
ሲቀረው የሚዘጉ ሲሆን የአንደኛ ማዕረግ (የክላውድ ናይን) ካውንተሮቻችን ደግሞ በረራው 45 ደቂቃ ብቻ
እስኪቀረው ድረስ ክፍት ሆነው ይቆያሉ። ስለዚህ ካውንተሮቹ ከመዘጋታቸው በፊት መገኘት አስፈላጊ ነው።
በዋሺንግተን ዲሲ ዳላስ ኤርፖርት ደግሞ መንገደኞችን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማስተናገድ እና ለሴኩሪቲ ፍተሻ
በቂ ጊዜ እንዲኖር መንገደኞች ከበረራው መነሻ ሰዓት አራት ሰዓት በፊት ኤርፖርት ላይ እንዲገኙ
እናሳስባለን። የኢትዮዽያ አየር መንገድ ከበረራው መነሻ ሁለት ሰዓት አርፍደው የመንገደኞች መቀበያ
ካውንተሮች ላይ የሚመጡ መንገደኞችን፤ የተረጋገጠ ምዝገባና ቲኬት ቢይዙም ያለማሳፈር መብቱ የተጠበቀ
ነው።
10. በአሜሪካ የጉምሩክ ህግ መሠረት፣
ሀ. ማንኛውንም የእንስሳ ስጋ፣ ቋንጣ ጭምር (ከበሰለ ዶሮና አሣ በስተቀር) እንዲሁም ፍራፍሬ፣
ቅጠላቅጠሎች፣ ዕፅዋት እና አፈር ወደ አሜሪካ ሀገር ይዞ መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው። ከላይ
የተጠቀሱትን ይዘው ቢገኙ ከፍተኛ ቅጣት የሚያስከትል መሆኑን እናሳስባለን። ከዚህ ውጪ በርበሬ፣
ሽሮ፣ ቅቤ፣ ወዘተ… በአግባቡ ከታሸጉ ይዞ መጓዝ ይቻላል።
ለ. ማንኛውም መንገደኛ ከ10,000 (አስር ሺህ) የአሜሪካ ዶላር በላይ ገንዘብ ወይንም ቁሳቁስ ይዞ የሚጓዝ
ከሆነ ወደ አሜሪካን ሀገር ሲገባም ሆነ ሲወጣ መጠኑን ማሳወቅ ይጠበቅበታል። ይህንንም ለዚሁ ተግባር
በተዘጋጀው ፎርም ላይ ሞልቶ ማሳወቅ ይገባዋል።
11. የማንኛውንም ሃገር የጉምሩክ ህግ ባለማክበር መንገደኞች ለሚደርስባቸው ቅጣት ወይንም እርምጃ የኢትዮጵያ
አየር መንገድ ተጠያቂ አይሆንም።
12. ጉዞአችሁን ከዋሽንግተን ዲሲ ባሻገር የምትቀጥሉ መንገደኞች ከመነሻ ያስመዘገባችሁዋቸውን ሻንጣዎቻችሁን
በዋሽንግተን ኤርፖርት ውስጥ በጉምሩክ ካስፈተሻችሁ በኋላ ለተጨማሪ የሴኩሪቲ ፍተሻ በተዘጋጀው ቦታ
አስረክባችሁ ጉዞዋችሁን መቀጠል ይጠበቅባችኋል። ይህ ባይሆን ግን ሻንጣችሁ ወደኋላ እንደሚቀር ማስገንዘብ
እንወዳለን።
13. የሚያርፉበትን ሥፍራ (ቤት፣ ሆቴል ወዘተ…) አድራሻ እና የስልክ ቁጥር መያዝዎን አስቀድመው ያረጋግጡ።
አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርትም ሆነ ዋሽንግተን ዲሲ ሲደረሱ ይህንን ዝርዝር አድራሻዎን
በሚጠየቁበት ሰዓት ካላቀረቡ ካቀዱት በረራ ሊያስተጓጉልዎትና ወደ አሜሪካ ለመግባት ሊያስቸግርዎት
ይችላል።
ለተጨማሪ መረጃ የጉዞ ወኪልዎን ወይም በአቅራቢያዎ የሚገኘውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቲኬት ቢሮ
ይጠይቁ። በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድን ድህረ ገፅ በ www.ethiopianairlines.com ይጎብኙ።




Comments are Closed