የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ጣልያኗ ሚላን ከተማ ዳግም መብረር ጀመረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ጣልያኗ ሚላን ከተማ ዳግም መብረር ጀመረ


የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት አቋርጦት የነበረውን የጣልያን ሚላን በረራ ዳግም መጀመሩን አስታውቋል።

በኮቪድ-19 ምክንያት በጣልያን ሁለተኛ መዳረሻ ወደ ሆነችው ሚላን ተቋርጦ የነበረውን በረራ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ በማድረግ መጀመሩን ነው አየር መንገዱ ያስታወቀው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ10 አመታት በፊት በሐምሌ ወር ላይ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሚላን ከተማ በረራ የጀመረው።
Comments are Closed